አገልግሎቶቻችን

ስዊዲሽ በርን ኬይር ፋውንዴሽን በአፍሪካ አገራት በእሳት አደጋ የቃጠሎ ጉዳት ለደረሰባቸው የተሻለ የሕክምና ክትትልና ድጋፍ እንሰጣለን።

በአፍሪካ አገራት የእሳት አደጋን ተከትሎ ለሚደርስ የአካል ቃጠሎ ሕክምና ድጋፍ፣ ስልጠናና ማቋቋም ይደረጋል

የስዊዲሽ በርን ኬይር ፋውንዴሽን ለትርፍ ያልተቋቋመ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን አገልግሎቱም በአፍሪካ አገራት በእሳት አደጋ ቃጠሎ ለተጎዱና ከፍተኛ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ህመምተኞች በአስፈላጊ ሁኔታ ሁሉ ድጋፍና ህክምና እንዲያገኙ መርዳት ነው። አገልግሎታችንም በየአገራቱ በሚገኙ የጤና ተቋማት ስር የሚገኙ የእሳት አደጋ ቃጠሎ ድጋፍ ማዕከላትን መገንባት፣ ማደራጀትና አስፈላጊውን ስልጠና መስጠት ነው። አስፈላጊ ነግሮች ሁሉ ተሟልተው ሲግኙ በጤና ተቋማቱ ስር የሚገኙት የእሳት አደጋ ቃጠሎ ድጋፍ ማዕከላቱ ሙሉ ለሙሉ ኃላፊነቱን ይረከባሉ።

ግንባታ

ዘመናዊ የእሳት አደጋ ቃጠሎ ድጋፍ ማዕከልን ሰርቶ ለማስረከብ ተገቢ ቦታና አስፈላጊ ቁሳቁሶች ያስፈልጋሉ። ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ቀድሞውንም አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉ ማዕከሎችን ለማሻሻልና አድሶ ለተገቢው የእሳት አደጋ ቃጠሎ ድጋፍ ማዕከልነት ለማብቃት የገንዘብ ድጋፍ እናደርጋልን። ይህንንም በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ተግባራዊ አድርገናል። ሥራውም ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀው እ.ኤ.አ ሚያዚያ ወር 2020 ዓ.ም ነው። የቀጣዩ ግንባታ ፕሮጀክት ደግሞ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በቡሌ ሆራ ከተማ ይሆናል። ለግንባታውም ከከተማው የዩንቨርስቲ ሆስፒታል አጠገብ ቦታ የተገኘ ሲሆን ግንባታውም እ.ኤ.አ 2021 ሊጀመር ታቅዷል።

አቅርቦት

ሳልቬሽን አርሚን ከመሰሉ ከተለያዩ ድርጅቶችም ጋር በመተባበር አገልግሎት ላይ የዋሉ ግን ዘመናዊ የሆኑ የሕክምና መሳሪያዎችን በማቅረብ የሕክምና ዋርዶቹን እናግዛለን። የሕክምና ቁሳቁሶቹ ሳልቬሽን አርሚ ኤድ ከተለያዩ የስዊዲን ሆስፒታሎች የሚያሰባስባቸው ነው። የስዊዲሽ በርን ኬይር ፋውንዴሽን እነዚህን ቁሳቁሶች የያዙ ኮንቴነሮች ወደ አፍሪካ አገራት እንዲጛጛዙ የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል። የመጀመሪያው የተላከው ጭነት ኢትዮጵያ የደረሰው እ.ኤ.አ ህዳር 2020 ነበር። እ.ኤ.አ መጋቢት 2021 ሌላ የኮንቴነር ጭነት ከስዊድን ይላካል። ዕቅዱ በአመት ከሶስት እስከ አራት የሚሆኑ ተመሳሳይ ጭነቶችን መላክ ነው።

ስልጠና

የስልጠና ተነሳሽነት እንዲኖርና በኢትዮጵያ በሚገኙ የተለያዩ ሆስፒታሎች እና በኡፕሳላ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል በርን ኬር ማዕከል በሚስሩ የጤና ባለሙያዎች መካከል የልምድ ልውውጥ እንዲፈጠር ድጋፍ እናደርጋልን። እንዲሁም እንደ ሲ.ቢ.ሲ.ሲ.ኤፍ እና ኢንተርበርንስ ከመሰሉ ድርጅቶች ጋር በቅርበት በመተባበር በኢትዮጵያ በእሳት አደጋ ቃጠሎ የሚደርስ የአካል ጉዳትን ተከትለው የሚሰሩ የሥልጠና ጥረቶችን እንዲሁም ከአምሬኤፍ ጋር በመተባበር አደጋ ከመድረሱ በፊት የመከላከያ ሥራዎችን በተመለከተ የሚሰጡ ትምህርቶችን እንደግፋለን።