ስለ እኛ

የስዊዲሽ በርን ኬይር ፋውንዴሽን ከኖርዌይጃን ችልድረን በርን ኤንድ ውንድ ኬር ፋውንድሽን ጋር በቅርበት በመተባበር በአፍሪካ አገራት የሚገኙ የእሳት አደጋ ቃጠሎ ድጋፍ ማዕከላትን በስልጠና እንዲሁም የማቋቋም ድጋፍ ይሰጣል። ተቋማችን ለትርፍ ያልተቋቋመ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን አላማችንም በአፍሪካ በእሳት አደጋ ቃጠሎ ምክንያት በየአምቱ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ በቂ የሕክምና ድጋፍና አቅርቦት በማጣት ከፍተኛ የአካል ጉዳት የሚደርስባቸውን ልጆች ከጉዳታችው በቶሎ እንዲያገግሙ መርዳት ነው።

ቦርድ

የስዊዲሽ በርን ኬይር ፋውንዴሽን የሚከተሉትን ባለሙያዎች ያካተተ ነው፥

Morten Kildal


ሜዲካል ዳይሬክተር ፣ ዶክተር ሞርተን ኪልዳል፣ በኡፕሳላ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል የበርን ኬይር ማዕከል የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና አማካሪ፣ እንዲሁም በኡፕሳላ ዩኒቨርስቲ የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ሲሆኑ በኢትዮጵያ በቃጠሎ የሚደርስ አደጋን ለማገዝ ለብዙ አመታት የጣሩ ባለሙያ ናቸው።

morten.kildal@brannskadefonden.se
+4670-333 71 55

Lasse Tenerz


ዶክተር ሌሰ ቴነርዝ የስዊዲሽ በርን ኬይር ፋውንዴሽን ሊቀመንበር ሲሆኑ እንደ ሀፒ ቻይልድ ሆም ፋውንዴሽን ባሉ ተቋማት የቦርድ ሃላፊነቶችን ከመወጣት ጀምሮ በተለያዩ ማህበራዊ ሥራ ፈጠራዎች ላይ ተሳታፊ ሲሆኑ እንዲሁም በታይላንድ አገር የወላጅ አልባ ህጻናትን የሚረዳ ድርጅት ይመራሉ።

lasse.tenerz@brannskadefonden.se
+4670-930 01 02

Ann Hammarstrand


አን ሀመርስትራንድ በስዊዲሽ በርን ኬይር ፋውንዴሽን የፋይናንስ ኃላፊ ሲሆኑ በህክምናው ኢንዱስትሪ ዘርፍ በፋይናንስ አስተዳደር ከፍተኛ የአመራር ዘርፍ የረጅም ጊዜ ልምድ ያዳበሩ ባለሙያ ናቸው።

ann.hammarstrand@brannskadefonden.se
+4673-316 10 65

Helena Tenerz


ዶክተር ሄሌና ቴንርዝ የፋውንዴሽኑ ፀሓፊ እና ቴክኒካል አማካሪ ሲሆኑ በሥራ ልምዳቸው የሜዲካል ቴክኖሎጂና የቢዝንስ ባለሙያ ናቸው።

helena.tenerz@brannskadefonden.se
+4670-830 01 02

Staffan Hällerfors


ስታፋን ኸለርፎርሽ የፋውንዴሽኑ የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ሲሆኑ በቀድሞ ሥራቸውም በመገናኛ ብዙኋን እንዲሁም በማርክቲንግና ሽያጭ ወይም ሴልስ አስተዳዳሪነት አገልግለዋል።.

staffan.hallerfors@brannskadefonden.se
+4670-773 45 48


Children's Burn & Wound Care Foundation, CBWCF

የስዊዲሽ በርን ኬይር ፋውንዴሽን ከኖርዌይጃን ችልድረን በርን ኤንድ ውንድ ኬር ፋውንድሽን ጋር በቅርበት በመተባበር በአፍሪካ አገራት የሚገኙ የእሳት አደጋ ቃጠሎ ድጋፍ ማዕከላትን በስልጠና እንዲሁም የማቋቋም ድጋፍ ይሰጣል።