በአፍሪካ አገራት የእሳት አደጋን ተከትሎ ለሚደርስ የአካል ቃጠሎ አደጋ ሕክምና ድጋፍ፣ ትምህርትና ማቋቋም

በታዳጊ አገራት በእሳት ቃጠሎ የሚደርስ የአካል ጉዳት አጣዳፊ የህክምና ድጋፍ ከሚያስፈልጋቸው ሕክምናዎች አንዱ ነው። በዚህ አደጋ ሴቶችና ህፃናት የበለጠ ተጎጂዎች ናችው። በዚህ አደጋ ሴቶችና ህፃናት የበለጠ ተጎጂዎች ናችው።

አገልግሎቶቻችን

የስዊዲሽ በርን ኬይር ፋውንዴሽን ለትርፍ ያልተቋቋመ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን አገልግሎቱም በአፍሪካ አገራት በእሳት አደጋ ቃጠሎ ለተጎዱና ከፍተኛ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ህመምተኞች በአስፈላጊ ሁኔታ ሁሉ ድጋፍና ህክምና መስጠት ነው። ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ደግሞ ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራው በየአገራቱ የሚገኙ ሆስፒታሎች የራሳቸውን የእሳት አደጋ ቃጠሎ ድጋፍ ማዕከል እንዲያቋቁሙ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ነው። እነዚህ እያንዳንዳቸው ሆስፒታሎች የሚያስተናግዷቸው ሰዎች ቁጥር ከስዊዲን የአጠቃላይ የሕዝብ ቁጥር ጋር የሚመጣጠን ይሆናል።

 

ድጋፍ ለማድረግ

ባንክ፥ SEB
አድራሻ፥ SEB 106 40 ስቶኮልም
የአካውንት ቁጥር፥ 5399 10 228 50
IBAN፥ SE5850000000053991022850
BIC ESSESESS

ስለ እኛ

የስዊዲሽ በርን ኬይር ፋውንዴሽን ከኖርዌይጃን ችልድረን በርን ኤንድ ውንድ ኬር ፋውንድሽን ጋር በቅርበት በመተባበር በአፍሪካ አገራት የሚገኙ የእሳት አደጋ ቃጠሎ ድጋፍ ማዕከላትን በስልጠና እንዲሁም የማቋቋም ድጋፍ ይሰጣል። ተቋማችን ለትርፍ ያልተቋቋመ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን አላማችንም በአፍሪካ በእሳት አደጋ ቃጠሎ ምክንያት በየአምቱ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ በቂ የሕክምና ድጋፍና አቅርቦት በማጣት ከፍተኛ የአካል ጉዳት የሚደርስባቸውን ልጆች ከጉዳታችው በቶሎ እንዲያገግሙ መርዳት ነው። በቀጣዩ ቪድዮ የስዊዲሽ በርን ኬይር ፋውንዴሽንን ከመሰረቱት ባለሙያዎች አንዱ የሆኑት ሜዲካል ዳይሬክተር፣ ዶክተር ሞርተን ኪልዳል የድርጅታችንን አላማ ኢንዲህ ይገልፁታል። 

አጋሮቻችን

በርካታ ተቋማትና ድርጅቶች በአፍሪካ አገራት የሚገኙ ታዳጊዎችንና ህፃናትን በማገዝ ትልቅ ለውጥ ለማመጣት ይችላሉ። ይህን መሰሉ አስተዋጽኦ እያንዳንዱ ሰው ለወደፊት በበለጠ የተሻለ ሕክምና የሚያገኝበትን ዕድል ለመፍጠር ይረዳል። የስዊዲሽ በርን ኬይር ፋውንዴሽን በአሁኑ ሰዓት ከተለያዩ በርካታ አጋሮቹ ጋር በመተባበርና ተጣምሮ በመስራት በእሳት አደጋ የቃጠሎ ጉዳት ለደረሰባቸው በሕክምናና ክትትል ድጋፍ ከፍተኛ አስተዋጻኦ አድርጛል።

በእሳት አደጋ ቃጠሎ የሚደርስ የአካል ጉዳት “ገንዘብ የሌላቸው ሰዎች በሽታ” ተደርጎ ይታሰባል፤ ነውም። እንደ አዓም አቀፉ የጤና ድርጅት ገልጻ “የተረሳው የዓለማችን የጤና ቀውስ ነው።”

 

0 ሚሊዮን
ስዎች በእሳት አደጋ ቃጠሎ የአካል ጉዳት ይደርስባቸዋል
0 በመቶ
የሚሆኑት ምንም አይነት የሕክምና ድጋፍ በማይሰጥባቸው አገራት ይኖራሉ
0
ሰዎች በየአመቱ በእሳት አደጋ ቃጠሎ ሕይወታቸውን ያጣሉ
0 በመቶ
ዎቹ ህፃናት ናቸው